Dr. Aregawi Berehe analyses the TPDM current situation-VOA Amharic…የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ጥቂት የድርጅቱን ታጣቂዎች ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ድርጅቱን “ከመጉዳት ይልቅ ያጠናክረዋል” ሲሉ የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ እና ከፍተኛ የአመራር የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ለቪኦኤ በሰጡት ትንተና ገለፁ።”አቶ ሞላ ቀድሞም ጫካ የገባው ሊታገል ሳይሆን ሊሰልል ነው።ሰውየው ለመንግስትም ቢሆን አይጠቅምም የአንድ ሳምንት ፉከራ ከመሆን በስተቀር”ብለዋል።
በሌላ በኩል የትሕዴን ምክትል ሊቀመንበር አቶ መኮንን ተስፋዬ ከአቶ ሞላ ጋር ከወጡት መካከል አሁንም ሱዳን ውስጥ ያሉትን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ለሬዲዮው ተናግረዋል፡፡
ሙሉውን የሬዲዮውን የድምፅ መረጃ ያዳምጡ።
↧
Dr. Aregawi Berehe analyses the TPDM current situation-VOA Amharic
↧